ውቢቱዋ ጨረቃ
ጥርት ባለው ሰማይ
አምራና አሸብርቃ
ስትታይ በሙሉ
ከዋክብት ፈዘው
በግርምት ያያሉ፣
እሱዋ ስትሰወር
የሰማዩም አድማስ
ሲዋጥ በጨለማ
ከዋክብት በተራ
ሲቀልቱ እንደሻማ
ከጎን ተደብቃ
ትሽቀረቀራለች
ለዳግም ሽብረቃ፡፡
No comments:
Post a Comment